የፋሲካ ዝግጅት

ውድ የማህበራችን አባል፡

የማክበር ሰላምታችንን በማስቀደም፡

የቅድስት ማርያም ራስ አገዝ መረዳጃ ማህበር የምግባረ ሠናይ ኮሚቴ ባለፉት ሦስት ዓመታት የትንሣዔን በዓል ምክንያት በማድረግ ለሀገሩ እንግዳ ለሆኑና በተለያዩ ምክንያቶች እለቱን በብቸኝነት ለሚያሳልፉ ወገኖቻችን ባደረጋቸው ቤተሰባዊ የፋሲካ ዝግጅቶች በድጋፍ ሰጪነት (sponsorship) የተሳተፋችሁትን ሁሉ ከልብ እያመሰገንን ፈቃደኝነቱ እያላችሁ ዕድሉ ላልደረሳችሁ ደግሞ ይህ ዓይነቱ የምግባረ ሠናይ ተግባር ቀጣይ እንደመሆኑ መጠን ምንጊዜም አስተዋፅዖ ማድረግ እንደምትችሉ በትህትና እንገልፃለን። በዚህም አጋጣሚ እስካሁን በተደረጉት ዝግጅቶች ታዳሚ የነበሩ ተጋባዦች የተሰማቸውን ስሜትና ከመስተንግዶው ያገኘነው ምላሽ ምን እንደሚመስል ለማወቅ መጓጓታችሁ አይቀርም።

እናም ጥሪው የፋሲካ በአል ምሳ እንደመሆኑ መስተንግዶው ለበዓሉ የሚስማሙ በዓይነት የተሠሩ የሀገራችን የባህል ምግቦችና ለማወራረጃ የሚሆኑ ለስላሳና መለስተኛ መጠጦችን በማካተት በባህላዊ ቡናና ቁርስ ስነ ሥርዓት የታጀበ ነው። ይህንንም ተከትሎ በቤተሰባዊ የዓመት በዓል ጨዋታ መሠረት የትውውቅና የልምድ ልውውጥ ውይይቶች የሚካሄዱ ሲሆን ይህም እንግዶቹ ስለ በዓሉ የተሰማቸውንና ለሀገሩ እንግዳ ሆነው ያጋጠማቸውን ለመግለጽ ያስችላቸዋል።

በመሆኑም ባለፉት የልምድ ልውውጥ ውይይቶች ቀደም ሲል የመጡና በተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ አልፈው በሕክምና በዳኝነት በጥብቅና በምህንድስና በምርምርና በማህበራዊ አማካሪነት ሞያዎች ላይ የተሰማሩ ወገኖቻችን ከራሳቸው ልምድ በመነሳት ጠቃሚ ምክሮችን ያካፈሉ ሲሆን እንግዶቹም እንደዝንባሌያቸው ጥያቄ በማቅረብ ሁኔታው እንደፈቀደ መልስ ተሰጥቶእል። በጥቅሉም የፋሲካው ጥሪ ቀድሞውኑ ያልጠበቁትና ከወገኖቻቸው ጋር ተሰብስበው ገበታ መሳተፋቸው የበዓል ቀን ብቸኝነታቸውን ምን ያህል እንዳስረሳቸውና የልምድ ልውውጡም “እኔም እችላለሁ” የሚል ተስፋ እንዳጫረባቸው በስሜት በመግለጽ ተግባሩ መበረታታት እንዳለበት በአጽንዖት ገልፀዋል።

ታዲያ በዚህም ዓመት ይህንኑ በቤተሰባዊ መንፈስ የትሞላ የፋሲካ መስተንግዶ ሚያዝያ ፳ ቀን ፳፻፲፩ ዓ/ም (April 28, 2019) በተመሣሣይ ሁኔታ የምናዘጋጅ ስለሆነ መደገፍ የምትፈልጉትን ሰው ቁጥር (በሰው $15 ሂሳብ) በመጥቀስ በጎ ፈቃዳችሁን በስልክ ቁጥር፡

(647) 865-1641 (ለወ/ሮ መቅደላዊት አበበ) ወይም

(416) 807-9471 (ለወ/ሮ ፋሲካ ሲሣይ) ትገልጹ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።


ከአክብሮት ጋር

የቅድስት ማርያም ራስ አገዝ የመረዳጃ ማህበር


Election Results

Executives Committee MembersPosition
Dr. Yohannis TadessePresident
Ato Daniel AsressVice President
Wro. Fasika SisayeSecretary
Ato Fiseha WeldoTreasurer
Ato Assefa NigusseAssistant Treasurer
Wro. Banchi TamratPublic Relations Officers
Wro. Wagaye LeggesePublic Relations Officers
Standby Members
Dr. Tewdros Kitawe
Ato Shirfrew Siraye

Council of Elders
Engineer Dereje Tafesse
Ato Surafel Hiruye
Dr. Kess Mebratu Kiros
Standby Members
Dr. Mezmur H/Meskel

Executives Committee Members


Wro. Banchi Tamrat

Ato Fiseha Weldo

Dr. Yohannis Tadesse

Ato Daniel Asress

Ato Assefa Nigusse

Wro. Fasika Sisaye

Wro. Wagaye Leggese

Dr. Tewdros Kitawe

Ato Shirfrew Siraye

Council of Elders


Engineer Dereje Tafesse

Ato Surafel Hiruye

Dr. Kess Mebratu Kiros

Dr. Mezmur H/Meskel


Charity

In keeping with its vision and mission, the Association will assist those who need a helping hand (the homeless, the hungry...

Read more

Spiritual Support

The association will comfort and offer its condolences to the family and loved ones of the deceased member. Also, through...

Read more

Financial Support

In the event of death of a member in good standing, the association will assist in contributing towards..

Read more

Membership

Any one who wish to join the association is strongly encouraged to read the association by-law. The association by...

Read more